Sunday, 6 October 2013

ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ (በ-ኣብርሃም ያየህ-1)


http://www.awrambatimes.com/wp-content/uploads/Abrahame_vs_G7.pdf


ው ይ ይ ት 

ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ 
ክፍል ኣንድ 
መ ግ ቢ ያ 
(በ-ኣብርሃም ያየህ) 
መስከረም 24 ቀን 2006 ዓ.ም. (October 4, 2013) 
ማስታወሻ፤ በዚህ "መግቢያ" ፅሑፌና በቀጣዮቹ ተከታታይ ፅሑፎቼ፥ ገዢውን ፓርቲ የምጠቅሰው በኣህፅሮት "ወያነ" በማለት ይሆናል። ኣንዳንዶቹ እንደሚያስቡት 
"ወያነ" የሚለው ኣጠራር "ህወሓት"ን ብቻ የሚገልፅ እንደሆነና፥ ኣሁን ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ስርዓት መጠሪያው "ኢህኣዴግ" ነው በማለት ሲናገሩ ይደመጣሉ። ይህ 
ካለማወቅ የመነጨ ኣባባል ነው። "ኢህኣዴግ" የገዢው ቡድን ያማርኛ ቋንቋ መጠሪያው ሲሆን፥ ቡድኑ ራሱን በትግርኛ ቋንቋ የሚጠራው ደግሞ "ናይ ኢትዮጵያ 
ህዝቢታት ወያናይ ዴሞክራሲያዊ ግምባር" (ኢህወዴግ) በማለት ነው። "ወያናይ" የሚለው ቅፅል-ስም "ወያነ" ከሚለው ስም የፈለቀ ሆኖ "ኣብዮታዊ" የሚለውን ያማርኛ 
ቃል እንዲወክል በራሱ በገዢው ቡድን የተመረጠ ስያሜ ነው። ስለሆነም፥ በተለየ ምክንያት "ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ"ን ኣስመልክቼ ስጠቅስ "ህወሓት" በሚል 
ሲሆን፥ ገዢውን ቡድን "ኢህኣዴግ/ኢህወዴግ"ን ስጠቅስ ግን "ወያነ" በሚል ይሆናል። 

ይህ የሌሎች ቀጣይ ፅሑፎቼ መግቢያ፥ የግንቦት ሰባት ዋና ፀሓፊ ኣቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በያዝነው ኣዲስ ዓመት ዋዜማ 
ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ1
 ላይ ተመርኩዤ በሚቀጥሉት ሳምንታት በተለያዩ ርእሶች በተከታታይ ለማቀርባቸው መጣጥፎቼ 
ጠቃሚ መንደርደሪያ ነው። መጣጥፉ በተለይ የሚያተኩረው ከሃያ ዓመት በፊት የኤርትራን ነፃነት ኣስገኘ በተባለለት ህጋዊ ያልሆነ 
ሬፈረንደም ላይ ነው። ይህ ኣስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት፥ ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ ለሚደረግ ማንኛወም ግኑኝነት የሪፈረንደሙ 
ኣፈፃፀምና የወያኔ ስርዓት ለኤርትራ ነፃነት የቸረው እውቅና ህጋዊ ያለመሆኑን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝብ ኣስቀድሞ ማሳየት ኣስፈላጊ 
በመሆኑ ነው። ስለሆነም፥ ለወያኔ መሪዎች የረጅም ጊዜ ድብቅ ዓላማ ማሳኪያ ተብሎ፥ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ በወያነ መሪዎች 
የተስተናገደው የኤርትራ ሬፈረንደም ኣፈፃፀም ህጋዊነት ያልተላበሰ መኖሩን በሰነድ ኣስደግፌ እገመግማለሁ። ስለዚህ፥ የሁሉም ቀጣይ 
ስራዎቼ መጋቢና የጀርባ ኣጥንት የሆነው ይህ መግቢያ መጣጥፌ እጅግ ወሳኝ የሆነ ጭብጥ ያዘለ ስለሆነ፥ ኣንባቢዎቼ በጥሞና 
እንዲመለከቱት በቅድሚያ ኣስታውሳለሁ። 
የኤርትራ ነፃነት በተመለከተ የወያነ መሪዎችና ቲፎዞዎቻቸው
2
 ሁሌም ሊያስረዱን የሚፈልጉት፥ ኤርትራ ነፃነቷን ያገኘችው 
በነሱ ፍላጎት ሳይሆን ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በጦርነት ኣሸንፎ ኤርትራን ስለተቆጣጠረ ምንም ማድረግ የሚቻል ነገር ያለመኖሩን ነው። ይሁን 
እንጂ ይህ ትክክለኛ መግለጫ ኣይደለም። 

በመጀመሪያ ደረጃ፥ ሻዕቢያ ያሸነፈው (ይህ ቀረው የማይባል የወያነ ድጋፍ ታክሎበት) ደርግን ነው እንጂ የኢትዮጵያን 
ህዝብ አይደለም። ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ህዝብ ማሸነፍ እነደማይችል ደግሞ የባድመ ቁርቁስ በሚገባ ኣሳይቶን ኣልፏል። ቁርቁሱ ኣሳዛኝና 
ኣላስፈላጊ ባይሆንም። ከዚያ ባሻገር ደግሞ፥ የኤርትራም ይሁን የሌላ ኣገር ነፃነት በጡንቻ ሊረጋገጥ ኣይችልም። ምክንያቱም፥ በጡንቻ 
የተገኘ ነፃነት በጡንቻ ሊነጠቅ ይቻላልና። የወያነ ቁንጮዎች የኤርትራ ነፃነት በጡንቻ የተገኘ ነው የሚሉን ከሆነ፥ ዛሬ ኢትዮጵያ ከሻዕቢያ 
በበለጠ በኤኮኖሚዋና በመከላከያ ኃይሏ ጡንቻዋን ያፈረጠመች ኣገር ስለሆነች፥ የኤርትራን ነፃነት በኃይል መግፈፍ ትችላለች ብለን 
ልንደመድም እንችላለን ማለት ነው። ነፃነት በህግ ይረጋገጣል እንጂ በጉልበት ኣይገኝም። ሻዕቢያ የሬፈረንደም ሃሳብ ያቀረበውም የኤርትራን 
ነፃነት ህጋዊነት ለማልበስ ሲል ነው። በተቀረ፥ ኤርትራን በኃይል ተቆጣጥሬኣለሁና ደህና ሁኑ ብሎ በተሰናበተን ነበር። 

የኤርትራ ነፃነት በህግ ተረጋግጦ በዓለም ህብረተሰብ እውቅና ሊያገኝ የሚችለው ደግሞ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ በወከለው 
መንግስት ወይም ጉዳዩ በሬፈረንደም አማካኝነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቦ፥ ህዝቡ በቃን ኤርትራ ትሂድ ብሎ ሲወስን ብቻ ነው። 
የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ በሬፈረንደም ወይም በወከለው ፓርላማና መንግስት ኣማካኝነት እውቅና ካልሰጠ የኤርትራ ነፃነት ብሎ ነገር 

የለም። ከዚህ ኣካሄድ ውጭ፥ ነፃነት በጉልበት የማይገኝ መሆኑን ለማስረዳት ረጅም ርቀት መጓዝ ኣያስፈልገንም። በቀላል መንገድ ግንዛቤ 
ለማስጨበጥ ሁሉም የሚያውቀቀውን ኣንድ ተጨባጭ ምሳሌ ልጥቀስ። 

የቅርብ ጎረቤቶቻችን የሆኑት ሶማሊላንድና ፑንትላንድ በጡንቻዎቻቸው ከሶማሊያ ተለይተው (በኣንፃራዊ እይታ) 
ዴሞክራሲያዊ የሆነ ስርዓት መስረተው መኖር ከጀመሩ ዘመናት ኣስቆጥረዋል። ይሁን እንጂ፥ እንደ ወያነ ያለ እውቅና የሚሰጣቸው ለጋሽ 
ስርዓት ሞቃዲሾ ላይ ባለመኖሩ፥ ባንዴራቸውን በዓለም መንግስታት ግቢ ለማውለብለብ ኣልቻሉም። ኣይችሉምም። ስለሆነም፥ እኛ ለወያነ 
መሪዎች እያልን ያለነው፥ ጦር ሰብቃችሁ ለምን ኤርትራን ኣላስቀራችሁልንም የሚል ኣይደለም። እኛ የምንለው ያለ፥ የኢትዮጵያና የኤርትራ 
ህዝብ ዘላቂ ጥቅምና ህልውና ግምት ውስጥ ባላስገባና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሬፈረንደሙን ኣስፈፅማኋል፤ የህዝብ ውክልና ሳይኖራቸሁ 
ለኤርትራ ነፃነት እውቅና መስጠታችሁ ተገቢ ኣይደለም፤ ይህንን በማድረጋችሁ ደግሞ በሃገር ክህደት ወንጀል ተከሳችሁ ለፍርድ 
ትቀርባላችሁ የሚል ነው። 

ይህ ኣስደንጋጭ ክስ ነው። ስለሆነም፥ የእርቀሰላም መድረክ ይከፈትና የወያኔ መሪዎች በዚህ ጥፋታቸው ምክንያት 
ካለባቸው ጭንቀት የተነሳ ትግራይንም ገንጥለው የቀረችዋን ኢትዮጵያ እንዳይበታትኑብን መተንፈሻ እንስጣቸው እያልን ስንወተውት፥ 
እንደነ ስብሓት ነጋና በረከት ስምኦን ያሉ ኮሚኮች "የምን እርቀ ሰላም? የተጣላ ሰው የለም፥ ልዩነታችን የመስመር ልዩነት ነው፥" ወዘተ. 
እያሉ ይቀልዱብናል። ክሱ ግን የኔ ክስ ብቻ ኣይደለም። በተደራጁ ኃይሎች ጭምር፥ በምርጫ ማኒፌስቶ ተቀናብሮ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ 
ድምፅ ሰጥቶበት፥ በምርጫ-97 ቅንጅትን አንፀባራቂ ድል ለማስመዝገብ ያስቻለው ክስ ነው። የቅንጅት ማኒፌስቶ ካረቀቁ ክቡራን 
መሃንዲሶች ዶ/ር. ብርሃኑ ነጋና ኣቶ ኣንዳርጋቸው ፅጌ ዋናዎቹ ስለሆኑ፥ ይህንን ማኒፌስቶ ያዘለውን ኣስደንጋጭ ክስ እዚሁ መጥቀስ ኣግባብ 
ያለው ይመስለኛል። 133 ገፆችን ያካተተው የነ ዶ/ር. ብርሃኑና ኣቶ ኣንዳርጋቸው ቅንጅት የምርጫ ማኒፌስቶ በገፅ 82 "የሃገር ሉዓላዊነት 
መደፈር" በሚል ርእስ ስር ያሰፈረውን እንመልከት። (እጠቅሳለሁ።) 
"የወያኔ/ኢህኣዴግ ኣገዛዝ የመንግስትን ስልጣን በጠመንጃ ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሃገሪቱን ሉኣላዊነትና 
የህዝቡን ብሄራዊ ጥቅሞች ለውጭ ኃይል ኣሳልፎ በመስጠት በሃገሪቱ ታሪክ ወስጥ ታይቶ የማይታወቅና ወደር የማይገኝለት 
የክህደት ተግባር ፈፅሟል። የኤርትራን ግንጠላ የሚደግፍ ህዝበ ውሳኔ [ሬፈረንደም] እንዲደረግ የፈቀደው የኢትዮጵያን ጥቅም 
እንደሚጎዳ ኣስቀድሞ እያወቀና ሆን ብሎ ነው። የሃገሪቱን ጥቅሞች የሚከላከል፥ የህዝቡን ሃሳብና ፍላጎት የሚወክል በህዝብ 
የተመረጠ ህጋዊና ቋሚ መንግስት በሌለበት የሽግግር ወቅት የሻዕቢያን ሃሳብ ደግፎ ለኤርትራ ግንጠላ የተባበሩት መንግስታትና 
የኣፍሪካ ኣንድነት ድርጅት እንዲተባበሩ ማመልከቻ የፃፈውና ኢትዮጵያ ወስጥ ድምፅ ለሚሰጡ ኤርትራዊያን ዳስና ድንኳን 
ከማዘጋጀት ጀምሮ ጠቅላላውን ሂደት ስፖንሰር በማድረግ የግንጠላው ተዋናይ ሆኖ የከረመው ይህንን እንዲፈፅም የሚያስችል
ህጋዊ ውክልና ሳይኖረው ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚወክሉ ሃሳቦች በነፃነት እንዳይንሸራሸሩ መድረኩ ሁሉ በተዘጋበት 
ሆኔታ ከሻዕቢያ ጋር ተመሳጥሮ ከህዝቡ ፈቃድና እውቀት ውጭ ሂደቱ [የሬፈረንደሙ ሂደት] የሃገሪቱን ጥቅም በሚጎዳ መንገድ 
እንዲከናወን ኣደረገ። ህዝበ ውሳኔው [ሬፈረንደሙ] ከመካሄዱ በፊት መፍትሄ ማግኘት የነበረባቸው የድንበር ጉዳይ፥ የባህር ቤት 
ባለቤትነት ጉዳይ፥ ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራዊያን ጉዳይ ምንም ዓይነት ትኩረት 
ኣላገኙም ነበር። በጣም የሚገርመው የኤርትራ ወረራ ዋዜማ ኣካባቢ የድንበር ጉዳይ ኣጨቃጫቂ ሆኖ ሲወጣ ጉዳዩ የሃገር መሆኑ 
ቀርቶ ከሻዕቢያና ከህወሓት ኣመራሮች የተወከሉ ኣባላት የሚገኙበት የድንበር ኮሚሽን ኣቋቁመው በምስጢር የሚደራደሩበት ሆኔታ 
ተፈጥሮ ነበር" (የጥቅሱ መጨረሻ፤ ኣፅንኦት/ሰረዝ የኔ።) 
የምፅኣቱ እንቆቅልሽ፥ ይህንን ክስ ሲደረድሩ የነበሩና፥ ምስኪን የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ልጆች ትርጉም በሌለው 
ጦርነት ወስጥ ተማግደው እንዲተራረዱ ሲደረግ ከወያነ መሪዎች ጎን ተሰልፈው ድንጋይ ያቀበሉት የግንቦት ሰባት ቱጃሮች ዛሬ ኣቶ ኢሳያስን 
የክርስቶስ ታናሽ ወንድም ነው ብለው የሚያቆላምጡና የሚክቡ ሰዎች ሆነው መገኘታቸው ነው። (ይህ ከባድ ክስ፥ በምርጫ-97 ማግስት 
የወያነ መሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሻዕቢያንም ያርበደበደ እንደነበረ በቀጣይ ፅሁፎቼ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በዝርዝር እመለስበታለሁ።)
3

"ኤርትራ ነፃነቷን የተቀዳጀችው በሻዕቢያ ጡንቻ ነው" የሚለው የወያኔ መሪዎች ጉንጭ ኣልፋ ኣሉባልታና የግንቦት ሰባቶች 
ትያትርዊ ተውኔት ወደጎን ትተን፥ ዛሬም፥ ሁልጊዜም፥ የኤርትራ ሬፈረንደም ኣፈፃጸም ጉዳይ የምናነሳው በወያነ መሪዎች መልካም ፈቃድና 
ፍላጎት የተቸረውና፥ በዓለም መንግስታት እውቅና የተሰጠውን የኤርትራ ነፃነት ለመቀናቀን ኣስበን ኣይደለም። የኤርትራን ሬፈረንደም እንደ 
ኣንድ ዋቢ ጉዳይ አድርገን የምናነሳበት ልዩ ምክንያት ኣለን። ባንድ በኩል የወያኔ መሪዎችን ማንነት ለህዝባችን የምናጋልጥበት ጉዳይ ስለሆነ 
ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፥ የስጋ ዘመዳሞች የሆኑትና የጋራ ጂኦ-ፖለቲካዊና ስትራተጂካዊ ጥቅሞችና ችግሮች ያሏቸው የኢትዮጵያና 
የኤርትራ ህዝቦች፥ ያለ ምንም ተጨማሪ ጦርነትና እልቂት፥ ሁሉንም በሚያረካ ሆናቴና፥ በሰላማዊ መንገድ ኣሁን ከገቡበት ኣዘቅት 
ማስውጣት ይቻላል ከሚል ፅኑ እምነት ተነስተን፥ ከዚሁ በተያያዘ ሬፈረንደሙ ህጋዊ ያለመኖሩን ለኤርትራ ህዝብ ጭምር ማስረዳት 

ለጉዳዩ ፋይዳ ያለው ግብኣት በመሆኑ ብቻ ነው
ከዚህ በተጨማሪ፥ የወያነ ኣመራር፥ ያለ ህዝብ ውክልና ያስፈጸመው ሬፈረንደም የኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ስላልሰጠውና 
ስለማይሰጠው፥ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር፥ በረጅሙ የኤርትራን ህዝብ ኣደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነም ጭምር ነው። ሻዕቢያም ይህንን 
በሚገባ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ትርጉም በሌለው ጦርነት ገብተንና ከወያኔ መሪዎች ጎን ተሰልፈን የኤርትራን ህዝብ ከምንወጋ ሌላ ነገር 
እንዘይድ ብለን እኛ ከኤርትራ ጋር ውይይታችን የከፈትነውም ከዚሁ ጭብጥ ተነስተን ነው። (ይህንን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት 
በሚለቀቀውና "ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ ጋር የሚደረግ ግኑኙነትና ትብብር ለምን?" በሚል ኣርእስት - በተራ ቁጥር 2 - በዝርዝር 
እመለስበታለሁ።) 

ስለዚህ፥ ከኤርትራ መንግስትም ሆነ ህዝብ ማንኛውም ዓይነት ውይይት የሚደረግ ከሆነ፥ የውውይቱ መክፈቻና 
መንደርደሪያ ይህ ህጋዊ ያልሆነ የሬፈረንደም ኣፈፃጸምና፥ ህዝባዊ ውክልና ያልነበረው የወያኔ ስርዓት ለኤርትራ የሰጠው እውቅና መሰረት 
በማድረግ መሆን ይኖርበታል። 

ይህ የሬፈረንደም ጉዳይ መነሳት ኣስፈላጊ ሆኖ ያገኘሁበት ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ፥ ኣቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፥ ከኢሳት ጋር 
ባደረገው ቃለ መጠይቅ፥ ከኤርትራ ጋር የሚደረግ ግንኙነት በሻዕቢያ ድጋፍ የወያነን ስርዓት ለማስወገድ ይቻላል በሚል እሳቤ ላይ 
ያነጣጠረ በመሆኑ ነው። ይህ በስልትም በስትራተጂም የተሳሳተ ስሌት ነው። በበኩሌ ከሻዕቢያ በሚገኝ ድጋፍ የወያነ ስርዓት ይሸነፋል 
የሚል ህልምም፥ ኣስተሳሰብም፥ ስሌትም የለኝም፤ ኖሮኝም ኣያውቅም። ወደ ኤርትራ ስሄድም ሆነ፥ "የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ 
ንቅናቄ፤ (ትህዴን)" ከሌሎች ጓዶች ጋር ሆነን ስንመሰረትም፥ የወያነን ስርዓት በሻዕቢያ ጠመንጃ መጣል እንችላለን ብለን ኣይደለም። 
የወያነን ስርዓት በቀላሉና ያለምንም ደም መፋሰስ ለማሰናበት የሚቻለው ከጠመንጃ ይልቅ ሌላ ህዝባችንና የመከላከያ ሰራዊታችንን በሚገባ 
የሚያሳምን ከጎናችን የሚያሰልፍ ነገር ከኤርትራ በኩል ማስገኘት ይቻላል ከሚል ስሌትና ጭብጥ በመነሳት ነው። (ትህዴን የመሰረትንበት 
ምክንያት በራሱ ሰፊ ታሪክ ያለው ስለሆነ በቀጣዩ ፅሁፎቼ በተራ ቁጥር 5 ይፋ የማደርገው ይሆናል።)
4


ከዚህ በተረፈ፥ የወያነን ስርዓት በሻዕቢያ ጠመንጃ መጣል የሚቻል ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች 
ተስማምተውበት፥ ኣምነውበትና ተካፍለውበት የሚደረግ እንጂ በግንቦት ሰባትና በትህዴን ሽርክና5
 ብቻ ሊከናወን ይቻላል ብሎ ማሰብ 
ኣይቻልም። እኔና መሰሎቼም "የሽማግሌዎች ምክር ቤት" ለመመስረት ያቀድነውና በዚያ ምክር ቤት ስር ሁሉም የተቃዋሚ ኃይሎች 
ለማሰባሰብ ብዙ የደከምነው፥ ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ በሚደረግ ግንኙነት የሚገኝ ፋይዳ ያለው ክንዋኔ ባንድ ወይም በሌላ ድርጅት 
ብቻ ሳይሆን ቢያንስ ወሳኝ የሆኑ የፖለቲካ ኃይሎች እንዲሳተፉበት በማስፈለጉ ነው። ምክር ቤቱን በሴራ ያፈረሱት በዚህ ሴራቸው 
ምክንያት ራሳቸውም የፈረሱ ቢሆንም፥ መንገዱ ግን እሱና እሱ ብቻ ነበር፤ ኣሁንም መንገዱ እሱ ነው። ስለሆነም፥ የትጥቅ ትግል ዝግጅት 
ማድረግ ያለው ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ፥ ከዚያ በላይ ግን ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት ላገራችንና 
ለህዝባችን የሚያመጣው ዘላቂ ጥቅምና ግኝት ያለው መሆኑን ህዝባችንና የመከላከያ ኃይላችንን በማያሻማ መንገድ በሚያሳምን ጭብጥ ላይ 
የተመሰረተ መሆን ኣለበት። (ይህንን ጭብጥ በተመለከተ በቀጣይ ፅሁፎቼ በተራ ቁጥር 2 "ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ ጋር የሚደረግ 
ግኑኝነት ለምን?" በሚል ርዕስ ይቀርባል።)
6


እዚህ ላይ ለማንም ሰው ግልፅ መሆን ያለበት ነገር፥ ሻዕቢያ ከኢትዮጵያዊያኖች ጋር የሚያደርገው ትብብር፥ ሻዕቢያ ራሱን 
ከመከራና ከውድመት ለማዳን ሲል እንጂ፥ ሻዕቢያ ኢትዮጵያንንና ህዝቧን ለመታደግ ወይም ለፅድቅ ብሎ የሚያደርገው ምንም ዓይነት 
ችሮታ የሌለ መሆኑን ነው። ከዚህ በተጨማሪ፥ በግልፅና በማያሻማ ቋንቋ መግለፅ የምንፈልገው፥ የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ ተጨባጭ፥ 
ኣስተማማኝና፥ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ የወያኔ ስርዓት በኢትዮጵያ ቤተመንግስታችን እንዲቆይ ለማድረግ የምንገደድ መሆኑን 
ነው። የወያነ ስርዓት የዲያብሎስ ስርዓት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን፥ ኣሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሆኔታና፥ የወያኔን መንግስት ሊተካ 
የሚችል ኣስተማማኝ ዝግጅት በሌለበት ወቅት፥ የወያነ ስርዓት ለኛ ኣስፈላጊ ዲያብሎስ (necessary evil) ነው። ወያኔን በቦታው 
ለማቆየት ደግሞ ከሁሉም ስራዎች የቀለለ የቤት ስራ ነው። ከባዱ የቤት ስራ፥ ያንገሸገሸንና ከተሰደድንበት ኣገር ሳይቀር እየተከተለ 
በሽብርተኝነት የሚከሰንን የወያነ ስርዓት ነቅሎ መጣል ብቻ ነው። 

ከሁሉ የከፋው ደግሞ፥ ኣያርገውና፥ ባንድ ወይም በሌላ ምክንያት፥ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ኣዲስ ጦርነት 
ቢቀሰቀስ፥ ይህን ጊዜ የኣብርሃም ያየህና የተባባሪዎቹ ጎዞ እንደትናንትናው ወደ ኣስመራ፥ ተሰነይ፥ ኣውጋሮና ሓሪና ሳይሆን፥ ወደ ኣዲስ-
ኣበባ፥ ዓዲግራትና ሸራሮ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ይህ ማለት፥ ከሻዕቢያ የሚለገስ የግንቦት ሰባት ጥይት ሰው የሚገድል 

ከሆነ፥ የመጀመሪያ ሟች ሰው የወያኔ ካድሬ ሳይሆን፥ "የቤቴ መቃጠል ለትኋኔ በጀኝ" የሚባል ፖለቲካ የማይዋጥለት ኣብርሃም ያየህ 














































No comments:

Post a Comment